2013 ሴፕቴምበር 4, ረቡዕ

መክሊታቸውን ለቀበሩ



1
እንደመድሀኒት አዋቂ ነን
የየሙያችን ’ኤክስፐርቶች’።
ለቤታችን አጥር ሰርተን፤
ለልባችን አጥር ሰርተን፤
ለዕውቀታችን አጥር ሰርተን፤
ዙሪያችንን በሾህ አጥረን
አልፎ ሂያጁን ተጠራጥረን
ከኮራጅ መሳይ ዕውቀት አሳሽ
ምስጢር ወሳጅ የልብ ወዳጅ
በር ዘግተን
ደጅ ቆልፈን
ያለን፤ እንደ መድሀኒት አዋቂ ነን!
2

በተክርስቲያንም - ቤተ እስልምና

ቤተመንግስትም - ቤተ ጎዳና
ቤተ ልሂቃንም -  ቤተ ፍልስፍና
ባንድ ደዌ ነው የተመታ፤
      ባንድ ልክፍት ነው የፀና!
3
ያደባባይ ሹሞች - ሆድ አደር ታጋዮች
የህብር እንግዶች - ዲስኩር አስደማጮች
ማንም የለ እንደኛ - ሕዝቡን አስደማሚ
መክሊቱን ቀባሪ ራስ አስታማሚ!
4
ሕመማችን ተመሳስሏል
ህልማችን ተኮራርጇል
አይሀኑ ሞን ሆኖብናል . . . 
ራሳችንን ሰስተነው
መውለድ ስንችል አስጨንግፈን
ጉድጓድ ምሰን ቀብረነዋል!
5
‘ብቸኛ’ መባል ሆነ ጌጣችን፤

      “አይተኬው ዕንቁ ፍጡር!”
     “አይጠጌው ጭንቂው ምሁር!”
ምኑጋ ነው ዕንቁነቱ
በምን ታይቶ ጭንቄነቱ
      ካላፈራ ደቀመዝሙር?

2 አስተያየቶች: